የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ዘወትር ተጠባቂውን “ወርቃማው ሰኞ” “Entrepreneurial College“ በሚል ርዕስ ውይይት አካሄደ
ህዳር/08/18ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፤ የወርቃማ ሰኞ የውይይት መድረክ የኮሌጁን ሰራተኞች ዘወትር ሰኞ ጠዋት 2፡00 ሰዓት በማሰባሰብ የሚደረግ ውይይት ሲሆን በያዝነው ሳምንት አለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ቀንን ምክንያት በማድረግ “Entrepreneurial College“ በሚል ርዕስ ውይይት ተካሂዷል በዚህም ኮሌጆች እንዴት “Entrepreneurial College“ ገጽታን መላበስ እንዳለባቸው የተነሳ ሲሆን ኮሌጆች የስራ ፈጠራ አስተሳሰብን በማዳበርና በመተግበር፤ የስርዓተ ትምህርትን ከገበያ ፍላጎት ጋር ማቀናጀት፣ ፈጠራን ለመደገፍ ከኢንዱስትሪዎች ጋር አጋርነት በመፍጠር ኮሌጃችን “Entrepreneurial College“ ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቶበታል፡፡
<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>

.