የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናወነ
አዲስ አበባ - የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ላይ ተሳትፏል። መርሀ ግብሩ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር ልዩ ስሙ ካራ መድሀኒአለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ተከናውኗል።
በዝግጅቱ ላይ የኮሌጁ ዋና ዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርአብዛ እና የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል። የችግኝ ተከላው በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል በተያዘው ሀገራዊ እቅድ ስር የሚካሄድ ሲሆን፣ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን ተሳትፈዋል።
ይህ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ኮሌጁ ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ፣ በሀገራዊ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስኬት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ለማበርከት ያለመ ነው።
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን



.