የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የንግድና ማህበራዊ ዘርፍ የቋሚ ኮሚቴ አባላት በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመስክ ምልከታ አደረጉ፤
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21/2018ዓ/ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ንግድና ማህበራዊ ዘርፍ የቋሚ ኮሚቴ አባላት በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመስክ ምልከታ አድርገዋል፤
የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ከሚሰጡ አገልግሎቶችና የሪፎርም ስራዎች አኳያ የኮሌጁ አሰልጣኝ፣ አስተዳደር ሰራተኞችና ሰልጣኝ ጉዳዮችን፣ በአደረጃጀትና በአሰራር የመጡ ለውጦችን ኮሌጁን ለአገልግሎት ምቹ ከማድረግ አኳያ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችንና አጠቃላይ የኮሌጁን የስራ እንቅስቃሴዎች ምልከታ አድርገዋል፤ በምልከታው ወቅት በኮሌጁ ከሚሰጡ ስልጠናዎች አኳያ የሆቴል ስልጠና ዘርፍ ወርክሾፖችን እና የስልጠና ክፍሎችን የጎበኙ ሲሆን።
ኮሌጁ አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ያለበትን የቦታ ሁኔታ ችግር ለመፍታት እንደሚሰራም አመላክተዋል፡፡



.