Announcement አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የዞኒንግና ዲፈረንሼሽን የአሰልጣኞች ዝውውርና ምደባ የሽኝትና አቀባበል እንዲሁም የ2017 በጀት አመት የዕውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የዞኒንግና ዲፈረንሼሽን የአሰልጣኞች ዝውውርና ምደባ የሽኝትና አቀባበል እንዲሁም የ2017 በጀት አመት የዕውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ

21st November, 2025

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የዞኒንግና ዲፈረንሼሽን የአሰልጣኞች ዝውውርና ምደባ የሽኝትና አቀባበል እንዲሁም የ2017 በጀት አመት የዕውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ


አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2018፤ አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የዞኒንግና ዲፈረንሼሽን የአሰልጣኞች ዝውውርና ምደባ የሽኝትና አቀባበል እንዲሁም የ2017 በጀት አመት የዕውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሂዷል፤

ፕሮግራሙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ከህሎት ቢሮ እየተገበረ የሚገኘውን የዞኒንግና ዲፈረንሼሽን የአሰልጣኞች ምደባ መሰረት በማድረግ ከኮሌጁ ወደ ሌሎች ኮሌጆች የተዘዋወሩ አሰልጣኞችና ወደ ኮሌጁ የተመደቡ አሰልጣኞችን እንኳን ደህና መጣቹ ለማለት የተዘጋጀ ሲሆን ኮሌጁ በ2017 በጀት አመት የላቀ አፈጻጸም ላመጡ የስራ ክፍሎችና ሰራተኞች የዕውቅናና ሽልማት ያበረከተበት ስነስርዓትንም ያካተተ ነበር፡፡

በዕለቱ የኮሌጁ ዋና ዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርአብዛ እንደገለጹት አሰልጣኞች በነበራቸው ቆይታ ለኮሌጁ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ያመሰገኑ ሲሆን በቀጣይ በተለያዩ ተቋማት በሚኖራቸው የስራ ቆይታ የተሻለ አብርክቶኦ እንዲኖራቸው አሳስበዋል፣ አያይዘው በኮሌጁ በ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም የላቀ አብርክኦ የነበራቸው የሥራ ክፍሎችና ሰራተኞች የነበራቸውን መልካም አፈጻጸም እንዲያስቀጥሉና ሌሎች ሰራተኞችም መነሳሳት እንዲኖራቸው አሳስበዋል፡፡

<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>

.

Copyright © All rights reserved.

Created with