Announcement የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በካይዘን ፍልስፍና መሰረት የስምንቱ ወርክ ስቴሽን ላይ ስራውን ለሚተገብሩ አሰልጣኞች የተግባር ስልጠና ሰጠ

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በካይዘን ፍልስፍና መሰረት የስምንቱ ወርክ ስቴሽን ላይ ስራውን ለሚተገብሩ አሰልጣኞች የተግባር ስልጠና ሰጠ

18th December, 2025

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በካይዘን ፍልስፍና መሰረት የስምንቱ ወርክ ስቴሽን ላይ ስራውን ለሚተገብሩ አሰልጣኞች የተግባር ስልጠና ሰጠ፤

ታህሳስ 09/2018ዓ/ም፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ፡ የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በካይዘን ፍልስፍና መሰረት የስምንቱ ወርክ ስቴሽን ላይ ስራውን ለሚተገብሩ አሰልጣኞች የተግባር ስልጠና ሰጠ፤ ይህ ስልጠና የወርክሾፖችንና አጠቃላይ የስራ ቦታዎችን በካይዘን ፍልስፍና መሰረት በስምንቱ ወርክ ስቴሽን አደረጃጀት በማደራጀት የላቀ አገልግሎት ለመስጠትና ቀጣይነት ያለው ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሰልጠና ፕሮግራሙ ኮሌጁ በሚቀጥሉት ወራት ከኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር ከእውነተኛው አለም የማምረቻ ፍላጎቶች ጋር መጣጣምን ለማረጋገጥና ሰልጣኞች ተገቢውን ክህሎት ለማዳበር ምቹ የስልጠና አካባቢ እንዲያገኙ ለማድረግና የአሰልጣኞችን ክህሎት ለማዳበር ያለመ ነው፡፡ የኮሌጁ የተቋም ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ም/ዲን ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው እንዳብራሩት የኮሌጁ አሰልጣኞችና መላው ሰራተኛ የካይዘን ፍልስፍናና ስምንቱን የወርክስቴሽን አደረጃጀቶች መተግበር የስራ አካባቢን ምቹ ከማድረግ ባለፈ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀጣይነት ያለውና ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ መሆኑን በመረዳትና በመተግበር ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with