የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክቶሬት የጥናትና ምርምር ስራዎች ግምገማ ተደረገ፤
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25/2018ዓ/ም በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በተካሄደው የጥናትና ምርምር ግምገማ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክቶሬት የስራ ክፍሎች የተጠኑ አራት የተጽዕኖና የዳሰሳ ጥናቶች ቀርበዋል።
በዚህም በዳይሬክቶሬቱ በምርታማነት ማሻሻያ፣በኢንተርፕራይዝ ድጋፍ እና በቴክኖሎጂ ድጋፎች ላይ ያተኮሩ የተጽዕኖና የዳሰሳ ጥናቶች ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች ጥናታቸውን በማቅረብ ከሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም ከኮሌጁ ባለሙያዎች የተነሱ ሀሳቦችን ወስደው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የኮሌጁ የኢንዳስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ም/ዲን አቶ ምስክር ኃ/እየሱስ እንዳብራሩት እንደዚህ አይነት የጥናትና ምርምር ስራዎች በተቋማት እና በኢንዱስትሪ አጋሮች መካከል ያለውን ትብብር አስፈላጊነት በማጉላት በኢንዳስትሪ ኤክስቴንሽን የሚሰጡ አገልግሎቶች ተገቢና ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡
ይህ የጥናትና ምርምር ግምገማም ፈጠራንና ቴክኒካል ክህሎቶችን በማጎልበት ቀጣይነት ያለው ውጤታማ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጅ ልማት አገልግሎት እንዲኖር ወሳኝ ነው፡፡
.