Announcement አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በመልካም አስተዳደር ጥናትና ምርምር ውጤቶች ላይ ስልጠናና ስርጸት መርሀ ግብር አከናወነ

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በመልካም አስተዳደር ጥናትና ምርምር ውጤቶች ላይ ስልጠናና ስርጸት መርሀ ግብር አከናወነ

18th November, 2025

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በመልካም አስተዳደር ጥናትና ምርምር ውጤቶች ላይ ስልጠናና ስርጸት መርሀ ግብር አከናወነ


ህዳር/08/18ዓ/ም፣ አዲስ አበባ፤ በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመልካም አስተዳደር ተግባራት ላይ የተደረገ ጥናት ቀርቦ የኮሌጁ የፕሮሰስ ካውንስል አባለት ውይይት ያደረጉበት ሲሆን በጥናቱ ግኝቶችም የስርጸት ስራ ተከናውኗል፡፡
ጥናቱ በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ያለውን የመልካም አስተዳደር ሁኔታ ከግልጸኝነት፣ ምላሽ ሰጪነት፣ የህግ የበላይነት እና የዜጎች ተሳትፎ አኳያ ያሉ ቁልፍ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ትኩረት በማድረግ የተከናወነ ሲሆን በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በዜጎች ተሳትፎ፣ በቢሮክራሲያዊ ቅልጥፍና እና ፍትሃዊ የአገልግሎት ተደራሽነት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበትም ተመላክቷል፡፡ በስርጸት መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዋና ዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርአብዛ እንዳብራሩት ኮሌጁ የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች፣ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች እና የኮሌጁ ነባራዊ ሁኔታ በተዋረድ ለሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብና ተገልጋይ ተመሳሳይ መረጃና ግልጸኝነት ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡


<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>

.

Copyright © All rights reserved.

Created with