Announcement የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ቀጥሏል...

የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ቀጥሏል...

02nd September, 2025

የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ቀጥሏል...

አዲስ አበባ

በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በመካሄድ ላይ ያለው የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር በስኬት ቀጥሏል። የኮሌጁን ማህበረሰብ የእውቀት አድማስ ለማስፋት ታስቦ የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር

ነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ ሰፋ ያለ የቡድን ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ላይ የኮሌጁ የአካዳሚክና የአስተዳደር ሰራተኞች በንቃት የተሳተፉ ሲሆን፣ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በሰፊው ተወያይተዋል። ከተሳታፊዎቹ በርካታ ገንቢና አዳዲስ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን፣ 

የቡድን ውይይቱ ተሳታፊዎች እርስ በእርስ ያላቸውን እውቀትና ልምድ እንዲለዋወጡ እንዲሁም የጋራ መግባባት ላይ እንዲደርሱ አስችሏል። ይህ ዓይነቱ መድረክ የሰራተኞችን የስራ ተነሳሽነት ከማሳደግ በተጨማሪ፣ ለኮሌጁ የልማት እቅድ ስኬት ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት ታምኖበታል።

የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር በቀጣይም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ውይይቶች በማዘጋጀት እንደሚቀጥል ታውቋል።

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን !

.

Copyright © All rights reserved.

Created with