በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር ተካሂዷል
አዲስ አበባ
በየሳምንቱ ሰኞ የሚካሄደው የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ዛሬ ነሃሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የተካሄደ ሲሆን መርሃ ግብሩ የኮሌጁን ማህበረሰብ የእውቀት እና አመለካከት በማሳደግና በማነቃቃት የተሸለ የመፈጸም አቅምና ተነሳሽነት እንዲዳብር ያደርጋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዋሬ ምክትል ዲን የሆኑት አቶ ተፈሪ ንጉሴ "Discipline" በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፍ ሰራተኞች በቂ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ወቅት "Discipline" በስራ ቦታና በግል ህይወት ውስጥ ያለውን ፋይዳ፣ ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ የሚጫወተውን ሚና እንዲሁም ውጤታማ የስልጠናና የስራ አካባቢ ለመፍጠር ያለውን ወሳኝነት በሰፊው አስረድተዋል።
ከኮሌጁ ማህበረሰብም በአቶ ኢምራን ሁሴን አነቃቂ ግጥም የቀረበ ሲሆን። ግጥሙ የወርቃማ ሰኞን መልካም ጅማሬ የሚያወድስ እና መርሃ ግብሩ ለኮሌጁና ለሀገር ዕድገት ያለውን አስተዋፅኦ የሚያመላክት ነበር።
የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር የኮሌጁን የአካዳሚክና የአስተዳደር ሰራተኞች የእውቀት ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉ ተከታታይ ውይይቶችን የሚያካሂድ መሆኑ ታውቋል። ይህ መርሃ ግብር የኮሌጁን ተልዕኮ በመደገፍና የስልጠና ጥራትን ለማሻሻል ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን



.