Announcement የ2018 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ከኮሌጁ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ተወያየ

የ2018 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ከኮሌጁ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ተወያየ

03rd November, 2025

ከአራዳ ማኑፋክቸሪንግ የ2018 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ከኮሌጁ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ተወያየ፤


አዲስ አበባ ጥቅምት 24፣ 2018ዓ/ም፡ አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን የሚገመግም አጠቃላይ የሰራተኞች መድረክ አካሄደ።

ውይይቱ በሩብ ዓመቱ የነበሩ ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞችን ለመገምገም፣ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና ስልታዊ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ አጠቃላይ የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የአስተዳደር ስራዎችን የሸፈነ ነበር፡፡
በውይይቱም ሰራተኞች ኮሌጁ አሁን ካለበት የስራ አፈጻጸም አኳያ የሰልጣኞች በምዘና የመብቃት ምጣኔን በተመለከተ አስተያየታቸውንና መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች ያነሱ ሲሆን በሌሎች ቀሪ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ የኮሌጁ ዋና ዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርዓብዛ እንዳብራሩት ኮሌጁ አሁን ካለበት የሩብ ዓመት አፈጻጸም አኳያ ብዙ መስራት የሚጠበቅበት መሆኑን በማንሳት በተለይም የመደበኛ ሰልጣኝ የመብቃት ምጣኔ በተመለከተ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with