Call us:
+929132651
|
Mail us for help:
aradamanufacturing@aatvetb.edu.et
|
Help center
360° Support - We are here to assist you.
Arada Manufacturing College
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
Support
Back
Support
Submit Ticket
My Tickets
More
Service
About
Contact Us
Status
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
Login
Announcement
በመትከል ማንሰራራት
በመትከል ማንሰራራት
18th August, 2025
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ሰራተኞች በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 "አረንጓዴ አሻራቸውን" አኑረዋል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም
የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ሰራተኞች ዛሬ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐግብር በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 "አረንጓዴ አሻራቸውን" አኑረዋል። የኮሌጁ ሰራተኞች ይህንን ተግባር ያከናወኑት "በመትከል ማንሰራራት" በሚለው መሪ ቃል መሰረት ሲሆን፣ አካባቢን የመጠበቅና የማልማት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ነው። በዚህ የችግኝ ተከላ መርሐግብር የኮሌጁ ሰራተኞች በንቃት በመሳተፍ በወረዳ 05 በሚገኙ ተስማሚ ቦታዎች ላይ 1500 ችግኞችን በመትከል የኮሌጁን ለአረንጓዴ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል። ይህ ተነሳሽነት በአካባቢው ያለውን አረንጓዴ ልማት ከማሳደግ ባለፈ፣ የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የዚህን መርህ ተፈጻሚነት በማረጋገጥ ለሀገራዊ የአረንጓዴ ልማት የራሱን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ይገኛል። በመርሐግብሩ ማጠናቀቂያም የኮሌጁ ሰራተኞች የችግኞቹን ስኬታማ እድገት ለማረጋገጥ የማያቋርጥ እንክብካቤ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
‘’ ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ ‘’
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
.